Fana: At a Speed of Life!

የአብኣላ ከተማ ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል አገኘች

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአብኣላ ከተማ እና አካባቢው ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የአብኣላ ከተማና አካባቢው በጦርነት ምክንያት በከተማዋ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ ከፍተኛ ውድመት በመድረሱ ምክንያት ኃይል ከሁለት ዓመት በላይ ተቋርጦ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

አገልግሎቱ እንደገና ለመመለስ በተደረገ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ጥገና ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግናኘት እንድትችል መደረጉን አገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተማው ከመቀሌ ሰብስቴሽን የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ሲያገኝ የነበረ ሲሆን÷ በጦርነቱ በደረሰ ከፍተኛ ጉዳት ተቋርጦ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይም የመከከለኛና የዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመሮችን እና ትራንስፈርመሮች እንደገና በመጠገን አገልግሎቱ ዳግም መመለስ ተችሏል ነው የተባለው፡፡

ቀሪ በኪልበቲ ረሱ የሚያገኙ ከተሞች ለማገናኘት እየተሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.