Fana: At a Speed of Life!

በሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ መጠነኛ የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ መጠነኛ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሚኒስትር አስታወቀ፡፡

ማሻሻያው በጀረጃ 1፣ ደረጃ 2 እና በደረጃ 3 ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ፥ በአስፋልት እና በጠጠር መንገድ ላይ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በዚህም መሰረት በደረጃ አንድ ተሽከርካሪዎች በጠጠር እና በአስፋልት ከነበረው ታሪፍ 6 በመቶ፣ በደረጃ  ሁለት 7 በመቶ እንዲሁም በደረጃ 3 ተሸከርካሪዎች በተመሳሳይ የ 7 በመቶ ጭማሪ ተደረጓል፡፡

የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በተቀመጠው ታሪፍ ብቻ በማስከፈል አገልግሎት እንዲሰጡ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ማሳሰቡን ከገጹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.