Fana: At a Speed of Life!

ሕብረተሰቡ የደም ልገሳ ባህሉን እንዲያሳድግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለመድረስ ሕብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን እንዲያሳድግ ጥሪ ቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሃብታሙ ታዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በመደበኛነት ከሚደረገው የደም ልገሳ በተጨማሪ የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ይካሔዳል፡፡

በዕለቱ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከሚከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር፥ 1 ሺህ ዩኒት ደም ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

በዚህም በጊዜያዊነት በሜክሲኮ፣ መገናኛ እና መርካቶ ምዕራፍ ሆቴል አካባቢ የሚገኙትን ዐደባባዮች ጨምሮ በጤና ሚኒስቴር ግቢ በሚገኘው የደም ባንክ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ግቢ የደምልገሳ ይከናወናል፡፡

ሌሎች በየአካባቢው ያሉ ቋሚ የደም መለገሻ ቦታዎች (ተቋማት) እንደተጠበቁ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በዓላት ተከታትለው ሲመጡ የደም ለጋሾች ቁጥር እንደሚቀንስ አስታውሰው፥ በጥር ወር ክብረ በዓላት ስለሚበዙ የደም እጥረት እንዳያጋጥም ሕብረተሰቡ በንቃት ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከሚሰበሰበው ደም በግጭት ምክንያት ሥራ ሳይሠሩ የነበሩ በትግራይ ክልል ለሚገኙ የደም ባንኮች ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የሕብረተሰቡ በመደበኛነት ደም የመለገስ ፍላጎት የበለጠ ማደግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.