Fana: At a Speed of Life!

ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ እና ድሬደዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች 66 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸው ተገለጸ፡፡

የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከታኅሣሥ 25 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ይዟል፡፡

በተመሳሳይ በድሬደዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከ54 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ በተለያዩ ኬላዎች መያዛቸውን የጉሙሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.