Fana: At a Speed of Life!

246 ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ባዛር በሐዋሳ ይከፈታል

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 246 ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ይከፈታል፡፡

ከጥር 4 እስከ 9 ቀን 2015ዓ.ም በሚካሄደው ኤግዚቢሽን እና ባዛር 246 ኢንተርፕራይዞች እንደሚሳተፉ እና ከ35 ሺህ በላይ ሰዎች እደሚጎበኙት ተጠቁሟል፡፡

በሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ‹‹በሀገሬ ምርት እኮራለሁ፤ ከሀገር ውስጥ አምራቾች እገዛለሁ›› በሚል መሪ ሐሳብ 246 ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከሚያደርጋቸው መንግሥታዊ ድጋፎች አንዱ÷ የገበያ ትስስር መፍጠር በመሆኑ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ኤግዚቢሽን እና ባዛር መዘጋጀቱን ነው የገለጹት፡፡

በበጀት ዓመቱ 600 ለሚሆኑ ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 18 ሚሊየን ብር ያህል የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ የሥራ ክኅሎት ሚኒስቴር እየሠራ ነው ብለዋል አቶ ንጉሡ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.