Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራ አደረጃጀቶች የዕውቅና መርሐ ግብር ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም የዳያስፖራ አደረጃጀቶች የዕውቅና መርሐ ግብር ሊካሔድ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ÷ ዳያስፖራው በተደራጀ መልኩ ያከናወናቸውን የፐብሊክ ዲፕሎማሲ፣ የገጽታ ግንባታ፣ የሀብት ማሰባሰብ ተግባራት እንዲሁም ያስገኛቸው ውጤቶችን ለማበረታታት መርሐ ግብሩ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡

በ25 ሀገራት የሚገኙና የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ከ40 በላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አደረጃጀቶች ዕውቅና እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል፡፡

አደረጃጀቶቹንና ያከናወኗቸው ተግባራት የሚያስተዋውቅ መጽሐፍ እንደሚመረቅ እና በማግስቱ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉብኝት ይኖራል መባሉን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጥላ ማኅበር መመስረት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ይፈረማል ተብሏል፡፡

የአይኤስ ፕሮሞሽንና ስፔሻል ኢቨንትስ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንድሪስ ቦንሱሩ ተቋማቸው በዳያስፖራዎች መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አይ ኤስ ፕሮሞሽንና ስፔሻል ኢቨንትስ መርሐ ግብሩን አዘጋጅተውታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.