Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው የተጠናቀቀው በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከልን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ- መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው የተጠናቀቀውን በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ፡፡
 
የማዕከሉን ቀሪ የግንባታ ስራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
 
በ90 ሺህ ሜትር ስኩዌር መሬት ላይ የተገነባው ማዕከሉ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን ፣ የመረጃ ፣ የላቦራቶሪ፣ የስልጠና፣ የኮንፈረንስ ማዕከል፣ ቢሮዎች እና አፓርታማዎችን እንዳሉት ተጠቁሟል፡፡
 
የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግንባታ ሲጠናቀቅ በህክምና መሳሪያዎች ከተሟሉ ማዕከላት አንዱ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን÷ ይህም በአህጉሪቱ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሏል፡፡
 
የማዕከሉ ግንባታ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ቻይና በ2020 የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ዋና መስሪያ ቤት ለመገንባት ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የተፈፀመ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 
 
በወንደሰን አረጋኸኝ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.