Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል ግንባታ እየተጠናከረ ለመጣው የአፍሪካና ቻይና ትብብር ዓይነተኛ ማሳያ ነው – የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ግንባታ እየተጠናከረ ለመጣው የአፍሪካና የቻይና ትብብር ዓይነተኛ ማሳያ ነው ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ገለጹ፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ዋና መስሪያ ቤት የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት ÷ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ግንባታ እየተጠናከረ ለመጣው የአፍሪካና የቻይና ትብብር ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡

ቻይና ለአፍሪካ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት፡፡

በተለይም በመንገድ መሰረተ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ድጋፍ ታደርጋለች ነው ያሉት።

በዓለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካ ሀገራት ተሰሚነት እንዲረጋገጥ ቻይና ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አንስተዋል።

በወንደሰን አረጋኸኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.