Fana: At a Speed of Life!

ፅንፈኛ ኃይሎችን በጋራ ለመታገል እንደሚሰሩ የኦሮሚያና አማራ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፅንፈኛ ኃይሎችን በጋራ ለመታገል እንደሚሰሩ የኦሮሚያና አማራ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አስታወቁ፡፡

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ እና የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ በአዳማ ሲካሄድ የቆየውን የፓርቲዎቹን የከፍተኛ አመራሮች ውይይት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

አመራሮቹ በባሕርዳር የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ በአዳማ በተካሄደው መድረክ ላይም የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሀገራችን ባለፈችበት ፈተና በሕዝብ የተገኘው ድል ሀገርን ማዳን ስለመቻሉ አፅንዖት መሥጠታቸው ተመላክቷል፡፡
በአንድነትና ወንድማማችነት መሥራቱ በመቀጠሉ አስፈላጊነት ላይ ውይይት መካሄዱም ተገልጿል።

በሁለት ቀናቱ ውይይት በጦርነቱ የደረሰውን ከባድ ጉዳት ከግምት በማስገባት አብሮ መስራት እንደሚያስፈልግና የመልሶ ማቋቋም ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል መወያየታቸውም ተነስቷል።

እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በጋራ መሻገር የሚቻለው በአንድነትና በወንድማማችነት መሆኑ መነሳቱንም አመራሮቹ ገልፀዋል፡፡

ለሰላም ማጣት ዋና ችግር እየሆነ የመጣውን ፅንፈኝነት ለመታገልም በጋራ መቆም እንዳለባቸው መምከራቸውንም ነው ያነሱት።

የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ላይም የጋራ አቋም ስለመያዛቸው ገልፀዋል።

መገናኛ ብዙኃን ከአላስፈላጊ ድርጊቶች ተቆጥበው የሀገር ግንባታ ስራዎች ላይ እንዲያተኩሩም ጥሪ አቅርበዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.