Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ሁሴን ሀሺ ቃሲም የሶማሌ ክልል የፍትህና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ ሞሃመድ ዶክተር ሁሴን ሀሺ ቃሲምን የክልል የፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አድርገው ሾሙ፡፡

ዶክተር ሁሴን በፐብሊክ ፖሊሲ የዶክተሬት ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፥ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፣ ከሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ ፣ ከያሌ ዩኒቨርስቲ እና ከኦታዋ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ስልጠናዎችን አግኝተዋል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከ19 ዓመት በላይ በአለም አቀፍ ልማት፣ በሰላም ግንባታ እና ፖሊሲ ትንተና ዘርፎች ሰርተዋል፡፡

እንዲሁም በሶማሌ ክልል የፀጥታ ሀላፊ ሆኖ ከመሾማቸው በፊት የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ከፍተኛ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል ፡፡

ዶክተር ሁሴን ከአለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች ጋር በምስራቅ አፍሪካ በመንግስት ግንባታ ፣ በአስተዳደር  እና በሰላም ግንባታ ረገድ ሰርተዋል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.