Fana: At a Speed of Life!

አሸናፊ በቀለ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸናፊ በቀለ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ በመሆን አፄዎቹን በይፋ ተረክበዋል፡፡

ፋሲል ከነማ በዘንድሮው የሊግ ውድድር ደካማ አቋም ያሳየ ሲሆን ፥ ባደረጋቸው 13 ጨዋታዎች 17 ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በዚህም ክለቡ የቡድኑን አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽን ቀደም ብሎ ያሰናበተ ሲሆን ፥ በምትኩ  አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የቡድኑ አሰልጣኝ በማድረግ ሾሟል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የቀድሞውን  መከላከያ ፣ ንግድ ባንክ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ጅማ አባጅፋርን በአሰልጣኝነት መርተዋል፡፡

አሰልጣኙ ቡድኑን በዛሬው ዕለት ልምምድ ማሰራት የጀመሩ ሲሆን ፥ በሀድያ ሆሳዕና እና ጅማ አባጅፋር በነበሩበት ወቅት ረዳት አሰልጣኝ ሆነው የሰሩት እያሱ መርሐፅድቅ  በረዳት አሰልጣኝነት አብረዋቸው እንደሚሰሩ ተመላክቷል።

ለሁለቱም አሰልጣኞች የክለቡ ደጋፊዎች ማኅበር በትላንትናው ዕለት በጎንደር ከተማ አቀባበል ያደረገላቸው መሆኑን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.