Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር አልጄሪያ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ውድድር አስተናጋጅ በሆነችው አልጄርያ በሰላም ገብቷል፡፡
 
ብሄራዊ ቡድኑ አልጀርስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአልጀርያ ባህላዊ ሙዚቃ የታጀበ አቀባበል ተደርጎለታል።
 
ዋልያዎቹ በቻን ውድድር በምድብ አንድ ከአዘጋጇ አልጄሪያ እንዲሁም ሞዛምቢክ እና ሊቢያ ጋር ተደልድለዋል።
 
ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከሞዛምቢክ ጋር የምታደርግ ይሆናል፡፡
 
በሀገር ውስጥ ሊግ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ሰባተኛው የቻን እግር ኳስ ውድድር በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ከጥር 5 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.