Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የቱሪዝም ዘርፍን ማነቃቃት ዓላማ ያደረገ “ድንቅ ምድር የዕውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓት” የፊታችን እሁድ ይካሔዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም “ድንቅ ምድር የዕውቅናና ሽልማትሥነ ስርዓት” እና “የወይዘሪት ቱሪዝም አማራ የቁንጅና ውድድር” በጎንደር ይካሔዳሉ፡፡

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበበ እምቢአለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ “ድንቅ ምድር የዕውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓት” እና “የወይዘሪት ቱሪዝም አማራ የቁንጅና ውድድር” በአጼ ፋሲል ቤተመንግሥት ግቢ ይካሔዳሉ፡፡

በ “ድንቅ ምድር የዕውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓት” ላይ÷ ቢሮው በሚያከናውናቸው 41 የባህልና ቱሪዝም ዘርፎች ዕውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች መወዳደራቸውን እና ባሸነፉበት ዘርፍ ዕውቅናው እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

ሌላው ዝግጅት “የወይዘሪት ቱሪዝም አማራ የቁንጅና ውድድር” መሆኑን ጠቁመው÷ ከአዲስ አበባ ከተማ፣ በአማራ ክልል ኪሚገኙ ሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አንደኛ የወጡ 33 ቆነጃጅት በባሕር ዳር ከተማ የአማራ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ስልጠና ሲሰጣቸው መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡

በስልጠናውም ከ33 ተወዳዳሪዎች መካከል በጎንደር ለሚካሔደው ውድድር 25 መለየታቸውን ገልጸው÷ በጎንደር ደግሞ 10 ተወዳዳሪዎች እስከሚቀሩ ድረስ አራት ዙር ውድድር እደሚካሔድ እና 10 ተወዳዳሪዎች ለመጨረሻ ዙር እንደሚቀርቡ ጠቁመዋል፡፡

ውድድሩን የምታሸንፈው ቆንጆም ‹‹የወይዘሪት ቱሪዝም አማራ›› አምባሳደር ሆና የክብር ዋንጫውን ትሸለማለች ብለዋል፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ጊዜም የአማራ ክልል የ2015 ዓ.ም የቱሪዝም አምባሳደር ሆና የምትቀጥል ይሆናል፡፡

ሌሎቹ ተሳታፊዎችም የየዞናቸው የቱሪዝም አምባሳደር እንደሚሆኑ አቶ አበበ አረጋግጠዋል፡፡

የአማራ ክልልን ባህል፣ አለባበስ እና ሌሎች ቱሪዝም ነክ ጉዳዮች በተለያዩ ዝግጅቶች የማሳየትና የማስረዳት ሥራ እንደሚጠበቅባቸውም ተመላክቷል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.