Fana: At a Speed of Life!

አጫጭር ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ መረጃዎች

 

  • ሊዮኔል ሜሲ ከዓለም ዋንጫ መልስ ለፒ ኤስ ጂ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል፡፡ ፒ ኤስ ጂ አንገርስን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ሜሲ በ72ኛው ደቂቃ አንድ ጎል አስቆጥሯል፡፡
  • ማንቼስተር ሲቲ በሳውዝሃምፕተን 2 ለ 0 ተሸንፎ ከካራባኦ ካፕ ውጭ ሆኗል፡፡ ኬቬን ዲ ቡርይና እና ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ ተጠባባቂ በሆኑበት ጨዋታ÷ ሳውዝሃምፕተን በሴኮ ማራ እና ሙሳ ጂንፖ ድንቅ ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
  • የአትሌቲኮ ማድሪዱ የፊት መስመር አጥቂ ዣኦ ፊሊክስ በውሰት ውል ቼልሲን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡ የ23 ዓመቱ ፊሊክስ በ11 ሚሊየን ፓውንድ የውሰት ውል ስታምፎርድ ብሪጅ የደረሰ ሲሆን÷ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ የሕክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
  • ቦሩሲያ ዶርቱመንድ ጃይደን ብራፍን እስከ ዓመቱ መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል ወደጣሊያኑ ክለብ ሄላስ ቬሮና መሸኘቱ ተሰምቷል፡፡ ደቻዊው ተጨዋች ከሌሎች ክለቦች ጥያቄ ቢቀርብለትም ወደ ጣሊያን ማምራትን ምርጫው ያደረገ ሲሆን÷ የሕክምና ምርመራውንም ነገ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን እና ቢ ቢ ሲ ስፖርት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.