Fana: At a Speed of Life!

ዕለታዊ አጫጭር የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎች

ቼልሲ ከ 17 ዓመት በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ በፉልሃም 2 ለ 1 ተሸንፏል፤የትላንት ምሽቱን ውጤት ተከትሎም አሰልጣኝ ግራም ፖተርስ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል፡፡

በጨዋታው የተሰለፈው አዲሱ ፈራሚ ዣኦ ፊሊክስ ለፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን ቢያደርግም ሜዳ ውስጥ በፈጸመው ጥፋት በ58ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ2022 የፊፋ ምርጥ የወንድ ተጫዋች እጩዎች ዝርዝር ውስጥ አለመካተቱ ተሰምቷል፡፡

ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔን ጨምሮ 14 ተጫዎቾቸ በተካተቱበት 2022 የፊፋ ምርጥ የወንድ ተጫዋች እጩዎች ዝርዝር ፖርቹጋላዊው ኢንተርናሽናል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሳይካተት ቀርቷል፡፡

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዩክሬናዊውን አጥቂ ማካሃይሎ ሙድራይክን ለማስፈረም ለሻካታር ዶኔስክ ሶስተኛ ይፋው የዝውወር ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል፡፡

አርሰናል ለዩክሬናዊው ኢንተርናሽናል ቅድሚያ የሚከፈል 70 ሚሊየን ዩሮ እና እየታየ የሚጨመር በቁጥር      ያልታወቀ የዝውውር ሒሳብ  ማቅረቡን ጎል ዶት ኮም አስነቧል፡፡

በፕረሚየር ሊጉ በነገው ዕለት በማንቹሪያ ደርቢ ማንቸስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ዘጠኝ ግቦች በተቆጠሩበት በመጀመሪው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ማንቼስተር ዩናይትድን 6 ለ 3 በሆነ ውጤት ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የቻን ውድድር እንደማይሳተፍ አስታውቆ የነበረው የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን በመርሐ ግብሩ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ወደ አልጀርስ እንደሚያቀና መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.