በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚገጣጠሙበት ፋብሪካ ከ3 ወራት በኋላ ሥራ ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠም የሚያስችል የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከሦስት ወራት በኋላ ሥራ ይጀምራል፡፡
በደብረ ብርሃን ከተማ ለተገነባው የኤሌክትሪክ መገጣጠሚያ ፋብሪካ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
የፋሪካው ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ፋብሪካው ከሦስት ወር በኋላ ወደማምረት ሥራ ይገባል፡፡
ፋብሪካው በዓመት 1ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም እንዳለው ገልጸው÷ ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሥራ ሲገባ በዚህ ዓመት ከ250 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንደሚገጣጠሙ ተናግረዋል፡፡
ፋብሪካው ለ500 ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተመላክቷል፡፡
በዘላለም ገበየሁ