Fana: At a Speed of Life!

ብሄራዊ ቡድኑ ከሞዛምቢክ ጋር ለመጫዎት ዝግጁ ነው – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት ከሞዛምቢክ ጋር ለሚደርገው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ፡፡

በነገው ዕለት የሚካሄደውን ጨዋታ አስመልክቶ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ መስኡድ መሐመድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ በመግለጫቸውም÷ ብሄራዊ ቡድኑ በሀገር ቤት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን እና ከጥር 4 ጀምሮ ወደ ሞሮኮ በማምራት ሁለት የዝግጅት ጨዋታዎችን ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ከትላንት በስቲያ አልጀሪያ መድረሱን ያነሱት አሰልጣኝ ውበቱ÷ ነገ ከሞዛምቢክ አቻው ለሚያደርገው ጨዋታም ቡድኑ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ አምበል መሱድ መሃመድ በበኩሉ ዋልያዎቹ  በሀገር ቤት እና በሞሮኮ ጥሪ የዝግጅት ጊዜ ማሳለፉን ጠቅሶ÷ሁሉም ተጫዎቾች በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግሯል፡፡

በአልጀሪያ ጥሩ የልምምድ ቦታ እና የሆቴል መስተንግዶ መኖሩን ያመላከተው መሱድ÷ በአስተናጋጅ ሀገር ምድብ ውስጥ መሆን ውድድሩን ሊያከብደው እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

ይሁን እንጂ የመጀመሪያውን ጨዋታ በነጥብ የምንጀምር ከሆነ በመድረኩ የተሻለ ውጤት ማስመዘገብ እንችላለን ነው ያለው፡፡

በተመሳሳይ የሞዛምቢኩ አሰልጣኝ ቺኪንዮ ኮንጄ እና የቡድኑ አምበል በሰጡት መግለጫ÷ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከኢትጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.