Fana: At a Speed of Life!

በፈረንጆቹ 2022 ሩሲያ እና ቻይና የ190 ቢሊየን ዶላር ግብይት መፈጸማቸው ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው የፈረንጆቹ በጀት ዓመት ሩሲያ እና ቻይና የ190 ቢሊየን ዶላር ግብይት መፈጸማቸው ተገለጸ፡፡

በሩሲያ እና በቻይና መካከል የተፈጸመው የንግድ ልውውጥ ካለፉት ዓመታት አንጻር ከፍተኛው እንደነበርም ተመላክቷል፡፡

ከ20 ከፍተኛ የቻይና የንግድ አጋሮች መካከል ሩሲያ ግንባር ቀደም መሆኗን የሀገሪቱ ጉምሩክ አስተዳደር ጨምሮ አስታወቋል ፡፡

ሞስኮ እና ቤጂንግ እስከ ፈረንጆቹ 2024 ድረስ የንግድ ትብብራቸውን ወደ 200 ቢሊየን ዶላር ለማሳደግ ዕቅድ መያዛቸው ይታወሳል፡፡

ከወዲሁ ዕቅዳቸውን ፈጥነው ማሳካት በመቻላቸው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቻይና አቻቸውን ሺ ጂንፒንግ በቅርቡ በበይነ-መረብ አግኝተው አወድሰዋልም ነው የተባለው፡፡

የቻይና ጉሙሩክ አስተዳደር ዝርዝር መረጃዎች እንደሚያሳዩት በፈረንጆቹ 2022 ቤጂንግ 76 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ሩሲያ ልካለች፡፡

ይህም ከ2021 አንጻር ሲቃኝ ከፍተኛው እንደሆነና የ12 ነጥብ 8 ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ሩሲያ በበኩሏ ወደ ቻይና የ114 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ምርቶችን በመላክ ወጪ ንግዷ በ43 ነጥብ 4 በመቶ ማደጉ ተመላክቷል፡፡

በታኅሣሥ ወር ብቻ ሀገራቱ የ17 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማካሄዳቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

ሀገራቱ በቀጣይ በተለይ በኃይሉ ዘርፍ የንግድ ግንኙነታቸውን ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.