Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ለሚካሔደው ሕዝበ ውሳኔ ለኦፕሬሽን ማስፈጸሚያ የሚያገለግሉ ቁሶች ተሰራጩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሔድ የሚያስችለውን ቁስ አሰራጨ፡፡

ቦርዱ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ ዞኖች እና ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ አሌ፣ ዲራሼ ልዩ ወረዳዎች ሕዝበ ውሣኔ ለማካሔድ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ ነው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያይዘ ሕዝበ ውሣኔውን በማስፈጸም ለሚሠማሩ ሠራተኞች የስልጠና ሠነዶችና ቁሶችን እንዲሁም በሕዝበ ውሣኔ ቀን በምርጫ ጣቢያ ላይ ለኦፕሬሽን ማስፈጸሚያ የሚያገለገሉ ቁሶችን ማለትም የድምፅ መስጫ ሣጥን እና የምስጢራዊ ድምፅ መስጠት ሂደቱን መከለያ ወደ ተመረጡ የሕዝበ ውሣኔ ማስተባበርያ ማዕከላት አሠራጭቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.