Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አየር ሃይል ታሪክ ጀብዱ ለፈፀሙ ጀግኖች የምስጋናና የእውቅና ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አየር ሃይል ታሪክ ጀብዱ ለፈፀሙ ጀግኖች የምስጋናና የእውቅና ስነ ስርዓት በቢሸፍቱ ከተማ ተካሂዷል።

የአየር ሃይል አባል የነበሩት ጀግናው ኮለኔል ባጫ ሁንዴ አፅም ከውጪ ሀገር ወደ ሀገር ሲገባ የአቀባበል ስነ ስርዓት ተካሄዷል።

በኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነት ኮ/ል ባጫ ሁንዴ በአየር ሀይል ተዋጊነታቸው ጀብድ በመፈፀም ታሪክ የሰሩ ጀግና ናቸው።

በጀግንነታቸውም የላቀ የጦር ሜዳ ሜዳይ ተሸላሚም ስለመሆናቸው የታሪክ ማህደራቸው ያሳያል።

ጀግናው ኮነሌል ባጫ ከ7 ዓመት በፊት በአሜሪካን ሀገር ህይወታቸው እንዳለፈ ይታወሳል።

በሌላ በኩል የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይርማ መርዳሳ፣ በአየር ሃይል ታሪክ ጀብዱ የፈፀሙ ጀግኖችና ቤተሰቦቹ እንዲሁም የቢሸፍቱ ነዋሪዎች በተገኙበት ለጀግኖች የምስጋናና የእውቅና ስነ ስርዓት ተካሄዷል።

ጀግኖች የሚከበሩት ጀግና ትውልድ ለመፍጠር መሆኑን  የተናገሩት ሌ/ጄነራል ይልማ÷በሁሉም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ጀግና አጥታ አታውቅምም ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ለጠላት የሚያስፈራ ለወገን በሚያኮራ መልኩ እየተገነባ መሆኑንም ገልፀዋል።

የኮ/ል ባጫ ሁንዴ አፅም በነገው ዕለት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን አጽማቸው በክብር እንደሚያርፍ መገለጹን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ  ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.