ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 206 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ያስመረቃቸው÷ በሕክምና፣ በተፈጥሮ ሣይንስ፣ በማኅበራዊ ሣይንስ እና በሌሎች የትምህርት ዘርፎች በተለያየ መርሐ ግብር ትምርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከል 296 ያህሉ በሕክምና ሲሆን÷ ይህም ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሐኪሞች ሲያስመርቅ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ከዛሬ ተመራቂዎቹ መካከል 24 ያህሉ በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርትታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ እንደገለጹት÷ የሕክምና ተመራቂዎች ከራስ በፊት ሕዝባቸውንና ሀገራቸውን በማስቀደም የገቡትን ቃል ኪዳን በትጋት እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በሙክታር ጠሃ እና አብዱራህማን መሃመድ