Fana: At a Speed of Life!

ወደ ኋላ የሚጎትቱንን የፖለቲካ ነጋዴዎች ያለምህረት እንታገላለን – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ልማታችንን እና ተጠቃሚነታችንን ለማደናቀፍ ወደ ኋላ የሚጎትቱንን የፖለቲካ ነጋዴዎችን ለህዝባችን ሰላምና ጥቅም ስንል ያለምህረት እንታገላለን ሲሉ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

የሲዳማ ክልል በክልሉ ልማት እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እየተወያየ ነው፡፡

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በውይይይ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሲዳማ ሕዝብ እራሱን በራሱ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብቱ ተከብሮለታል ብለዋል፡፡

ለረዥም ዘመናት ክልሉ ተነፍጎ የቆየውን ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እያገኘ ነው ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ልማታችንን እና ተጠቃሚነታችንን ለማደናቀፍ ወደ ኋላ የሚጎትቱንን የፖለቲካ ነጋዴዎችን ለሕዝባችን ሰላምና ጥቅም ስንል ያለምህረት እንታገላለን በአጽንኦት ገልጸዋል አቶ ደስታ፡፡

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ÷ አካታች የፖለቲካ ሥርዓት ሰፍኖ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ትግል ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.