Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ-ብርሀን የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ተወካዮችን አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ-ብርሀን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ተወካዮችን አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተገኝተዋል፡፡

በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም መንግስት በትኩረት ይሰራል ያሉት አቶ ደመቀ ፥ ጊዜያዊ ድጋፍም በፍጥነት ይደረጋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከብዙ ውጥረት ፋታ እያገኘች ስለሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈናቃዮች ተመልሰው እንዲቋቋሙ ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡

ሁሉም ዜጎች በሀገሪቱ የተለያዩ ማዕዘናት የመኖር ነፃነት አላቸው ያሉት አቶ ደመቀ ፥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደነባር ቦታቸው ተመልሰው እንዲኖሩ ሰላም የማስፈን ስራ ይሰራል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በፍቅርተ ከበደ እና ዘላለም ገበየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.