Fana: At a Speed of Life!

ድምፃዊት ያለምወርቅ ጀምበሩ የ3ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምፃዊት ያለምወርቅ ጀምበሩ የ3ኛው የፋና ላምሮት የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊ ሆናለች፡፡

3ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የድምፃውያን ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በዚህም ያለምወርቅ ጀምበሩ በአንደኝነት አሸናፊ ሆናለች።

እንዲሁም አሉላ ገ/አምላክ ሁለተኛ ፣ ዳንኤል አዱኛ በሦሥተኛ ደረጃ ሲያጠናቅቅ፣ ደሣለኝ አበበ አራተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

ለእያንዳንዳቸውም የ300ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡

የዓመቱን ሦስት ምዕራፎች በአሸናፊነት ያጠናቀቁ 12 ተወዳዳሪዎችና በልዩ ሁኔታ የተካተቱ ሁለት ተፎካካሪዎች በአጠቃላይ 14 ተወዳዳሪዎች ለ10 ሳምንታት ሲፎካካሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

በዚህም አራት ተወዳዳሪዎች ተለይተው በዛሬው ዕለት ደሳለኝ አበበ፣ አሉላ ገ/አምላክ፣ ዳንኤል አዱኛ እና ያለምወርቅ ጀምበሩ የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊ ለመሆን ብቃታቸውን ሲያሳዩ ቆይተዋል፡፡

በርካታ ተመልካቾችና አንጋፋ አርቲስቶች በተገኙበት በቀጥታ ስርጭት በተካሄደው የፍጻሜ ውድድርም አሸናፊዋ ተለይታለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.