Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደሮች የጎርጎራ ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን የሚወክሉ አምባሳደሮች የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የጎርጎራ ፕሮጀክት ጎበኙ፡፡

አምባሳደሮቹ ፕሮጀክቱ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን÷ የግንባታ ሂደቱን በተመለከተም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በጎርጎራ ፕሮጀክት የቱሪስት ፍሰትን ለመሳብና የአካባቢ ጸጋን በመጠቀም የተለያዩ ልማቶችን ለመተግበር መታቀዱ ይታወቃል፡፡

ዘመናዊ ካፌና ሬስቶራንት፣ የብስክሌትና ፈረስ መጋለቢያ፣ ባህላዊ መንደሮች ልማት፣ የግብርና ምርምር፣ የዓሳ ማስገሪያ መዳረሻን ማልማትና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.