Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ እና የሲዳማ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች  በወቅታዊ  ሀገራዊና ክልላዊ  ፖለቲካዊ ሁኔታዎች  እንዲሁም በሠላምና  ፀጥታ አዝማሚያዎች  ላይ በሀዋሳ ከተማ እየመከሩ ነው።

ክልላዊ  ወቅታዊ  ፖለቲካዊ  አዝማሚያዎችን እና የሠላምና የፀጥታ ሁኔታዎችን አመላከች  መነሻ ሀሳብ በክልሉ  ርዕሰ መስተዳድር  ርስቱ  ይርዳ ቀርቧል።

የአማራር መድረኩ በወቅታዊ  ሀገራዊና ክልላዊ  ፖለቲካዊ  አዝማሚያዎች ላይ  የጋራ አረዳድ  በመፍጠር  የተጀመረው  የሠላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ  ግንባታ  ሂደቱ   እንዲጠናከር  ፋይዳዉ የጎላ መሆኑ ተገልጿል ።

በተመሳሳይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡

በውይይት መድረኩ በሀገራዊ፣ ወቅታዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ አመራሮች ዝርዝር ውይይት እንደሚያካሂዱና የጋራ መግባባትላይ እንደሚደርሱ ይጠበቃል፡፡

በዚህም የህዝብ ተጠቃሚነት፣ ሀገራዊ አንድነትና ወንድማማችነትን በጋራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል አቅጣጠጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች ሀገራዊ ለውጡና የሰላም ስምምነቱ ዘላቂ እንዲሆን የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፈተናዎችን በመሻገር ድሎቻችንን እናፀናለን” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ  ሃገራዊ  ጉዳዮች ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።

በውይይቱ የክልል ፣የዞን የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን  በወቅታዊ ፖለቲካዊና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ሀገሪቱ  አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የፌድሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ  አገኘሁ ተሻገር  የውይይት መነሻ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

የዉይይት  መድረክ እስከ ነገ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.