Fana: At a Speed of Life!

የ24 ሀገራት አምባሳደሮች በደብረብርሃን ለኢንቨስትመንት ዝግጁ የሆኑ አካባቢዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የ24 ሀገራት አምባሳደሮች በደብረ ብርሃን ከተማ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
 
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ጉብኝቱ በደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢው ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ለማሳየት ያለመ ነው፡፡
 
በጉብኝት መርሐ ግብሩ አምባሳደሮቹ በከተማዋ ለኢንዱስትሪ የተዘጋጁ የፋብሪካ ክላስተር የመሬት ዞኖችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን አንስተዋል፡፡
 
መሬቶቹ በጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብና መጠጥ፣ በእንጨት እና ብረታ ብረት ስራ እንዲሁም በኬሚካል ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ አልሚዎች የቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
የተዘጋጀው የፋብሪካ ክላስተር መሬት ዞን ስፋትም 2 ሺህ ሄክታር በላይ ስፋት ያለው መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
የውጭ እና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በደብረ ብርሃን መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ አስፈላጊው መሰረት ልማትና ሌሎች አቅረቦቶች መሟላታቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
በጉብኝቱ የተሳተፉ አምባሳደሮችም ከሀገራቸው የሚመጡ ባለሃብቶች በከተማዋ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ እንደሚያሳውቁ ማረጋገጣቸውንም ተናግረዋል፡፡
 
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.