Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ተጠናቋል-የደቡብ ክልል ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲውል ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን አስታወቀ፡፡

በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በያዝነው ሣምንት የሚከበረው የጥምቀት በዓል ከከተራው ጀምሮ በሰላም ተከብሮ እንዲውል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀዋል፡፡

በሁሉም ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲውል ፖሊስ አጭር የጸጥታ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን አረጋግጧል፡፡

በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ሕብረተሰቡ እንደወትሮው ሁሉ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን እንዲቆም ኮሚሽኑ ጥሪ አቀርቧል፡፡

አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲያይም በ 0462212870 በመደወል ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች እንዲጠቁም ህብረተሰቡ ተጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል እንዲሆን ተመኝቷል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.