Fana: At a Speed of Life!

የዕለተ ሰኞ የውጭ አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች

ሞሮኮ ከቻን ውድድር ራሷን ማግለሏ ተሰምቷል፤ይህን ተከትሎም በቻን የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ከሞሮኮ ጋር ጨዋታ የነበራት ሱዳን በፎርፌ አሸንፋለች፡፡
 
የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት አቅም አለን ሲል ፈረንሳዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ተከላካይ ራፋይል ቫራን ተናግሯል፡፡
 
ቫራን ይህን ያለው በማንቹሪያ ደርቢ ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን በማሸነፍ ከመሪዎቹ አርሴናል እና ማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበቡን ተከትሎ ነው፡፡
 
ከአርሴናል ጋር መዋዳደር ከባድ ነገር ሊሆን ይችላል ያለው ቫራን ÷ ነገር ግን ፕሪሚየር ሊጉን ለማሸነፍ አሁንም ዕድል መኖሩን አመላክቷል፡፡
 
አርሰናል በበኩሉ÷ በሰሜን ለንደን ደርቢ ተጠባቂ ጨዋታ ቶተንሀምን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
 
ውጤቱን ተከትሎም አርሰናል ከሜዳ ውጭ ያደረጋቸው ተከታታይ አምስት ጨዋታዎችን ሳይሸነፍ መጓዝ ሲችል ፤ አሰልጣኙ ሚካኤል አርቴታም ከሜዳው ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ቶትነሃምን ማሸነፍ ችሏል፡፡
 
ማርቲን ኦዴጋርድ ደግሞ በፕሪሚየር ሊጉ ሲዝን ባደረጋቸው 17 ጨዋታዎች 8 ግቦችን እና 5 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል የክለቡ ባለውለታ መሆኑን ቀጥሏል፡፡
 
በስፔን ሱፐር ካፕ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል፤ በዚህም ስፔናዊው የካታሎኑ ክለብ አለቃ ዣቪ ሄርናንዴዝ ትናንት ምሽት ያሸነፈው ዋንጫ በክለቡ ቤት የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡
 
የቻን ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲደረጉ ምሽት 1 ሰዓት ማሊ ከአንጎላ፣ ምሽት 4 ሰዓት ደግሞ ካሜሮን ከዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.