Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ሕዝብ ቁጥር በ60 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሽቆልቆሉ ተነግሯል

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የሕዝብ ቁጥር ከ1961 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነስ እንደየታየበት ተገልጿል፡፡

ሀገሪቱ በታሪኳ በማኦ ዜዶንግ የግብርና ፖሊሲ አስከፊውን ረሃብ ስትዋጋ ካጋጠማት የህዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የቁጥር መቀነስ መመዝገቡ ተመላክቷል፡፡

በዓለም ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ላላት ቻይና ክስተቱ ታሪካዊ ሊባል እንደሚችል እና የሕዝብ ቁጥር መቀነሱ ከዚህ በኋላ ለረጅም ጊዜ ይዘልቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

በ2022 መገባደጃ ላይ የቻይናውያን ህዝብ 1 ቢሊየን 411 ሚሊየን 750 ሺህ በላይ እንደነበር የቻይና ብሄራዊ ስታቲስቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት መጨረሻ ጋር ሲነፃፀር በ850 ሺህ ቅናሽ እንዳሳየ መጠቆሙን አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል፡፡

በዓለም ለረጅም ጊዜ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ ሆና የቆየችው ቻይና በቅርቡ ሥፍራውን ከ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ የህዝብ ብዛት እንዳላት ለምትገመተው ህንድ ትለቃለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.