Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ፖሊስ ለጥምቀት በዓል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጥምቀት በዓልን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው÷ በዓሉ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡
ህብረተሰቡ ራሱን እና ቤተሰቡን ከትራፊክ እና እሳት አደጋ እንዲጠብቅም ነው ፖሊስ ያሳሰበው፡፡
በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር የሃይማኖት አባቶች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ በክልሉ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.