Fana: At a Speed of Life!

ቤተ ክርስቲያኗ ከ118 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚተገበር የልማት ስራ ይፋ አደረገች

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን በተለያዩ ክልሎች ላይ ተግባራዊ የሚሆንና በ118 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የልማት ስራ ይፋ አደረገች፡፡

በደቡብ ክልል አራት ወረዳዎችና በሲዳማ ሦስት ወረዳዎችን እንዲሁም በኦሮሚያ ተልተሌን መዓከል ያደረገ ፕሮጀክት በይፋ ስራ የማስጀመር ስምምነት ተደርጓል ።

ተግባራዊ በሚደረጉት ፕሮጀክቶች ሦስት አብይ ተግባራት የሚከወን መሆኑን የተናገሩት በኮሚሽኑ የፕሮጀክቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ አበያ ፥ በሰላም ግንባታ ፣በሴቶች አቅም ማጎልበትና የምግብ ዋስት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኮሚሽነር ዶክተር አበያ ዋቅወያ በበኩላቸው÷ ተቋሙ በሁሉም ክልሎች እየሰራ የሚገኝና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ270 ፕሮጀክቶች በላይ በተግባር ላይ እንደሚገኙም ነው የገለጹት ።

የ270 ፕሮጀክቶች አካል የሆኑ የተወሰኑ ፕሮጀክቶችን በሲዳማና ደቡብ ክልሎች ውስጥ ለመተግበር መፈራረማቸውን በመግለፅ በቀጣይም በሌሎችም ክልሎች ተግባራዊ የሚደረጉ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ለሦስት አመታት የሚቆይ ሲሆን ÷ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.