Fana: At a Speed of Life!

681 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሁለት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 681 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለፀ፡፡

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት ውስጥ 670ዎች ወንዶች እና 11 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 30 ሺህ 746 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.