Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ከቄለም ወለጋ ዞን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቄለም ወለጋ ዞን ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልለ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የመከላከያ መራሮች ፣ አባ ገዳዎች ፣የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ፥ መንግስት ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ለስኬታማነቱ ህብረተሰቡም የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል፡፡

የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አቶ ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው፥ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን መግለጻቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.