Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የስዊድን ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው ፥ የጥምቀት በዓልን ለሚያከብሩ የእምነቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ ብሏል፡፡

በተመሳሳይ የአውስትራሊያ ኤምባሲ ፥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ጥምቀት መሆኑን በመግለፅ ለእምነቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ ብሏል፡፡

በዓሉ ኢየሱስ ክርሰቶስ በዮሐንስ የተጠመቀበትን ጊዜ ለማስታወስ የሚደረግ መሆኑን የገለፀው ኤምባሲው ፥ የጥምቀት በዓል ከ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ይከበር እንደነበር አስታውሷል፡፡

የፈረንሳይ ኤምባሲ በበኩሉ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የጥምቀት በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡

የእስራኤል ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተከታዮች መልካም በዓል ተመኝቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.