Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ ባህረ ጥምቀት መከበር ጀምሯል፡፡
 
በዓሉ በካህናትና ዲያቆናት ዝማሬ እንዲሁም በሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
 
በበዓሉ ከ120 በላይ ካህናት ወረብና ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀርባሉ፡፡
 
መንበረ መንግስት መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል ስርዓት አድራሽ ነው።
 
በስርዓት ላይ ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የመጡ እንግዶች የውጭ ሀገራት ዜጎች ታድመዋል።
 
በመታገስ አየልኝ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.