Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡
 
በትግራይ በተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ መከበሩን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም አስተዳዳሪ ቆሞስ ንብረ ዕድ አባ መሀሪ ሀብቴ ተናግረዋል።
 
በአደባባይ የሚከበረው የጥምቀት ክብረ በዓል ከኃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ባህላዊ እሴቱን በጠበቀና ባመረ መልኩ እየተከበረ ቀጥሏል።
 
የጥምቀት በዓል ከአገራዊ ሃብትነቱም አልፎ የዓለም ቅርስ በመሆን በዩኔስኮ ተመዝግቦ የሚገኝ እሴት መሆኑ ይታወቃል።
 
በዓሉ በዛሬው እለት በመላ ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን በተጠበቀ መልኩ ተከብሯል።
 
በትግራይ ክልልም በደማቅ ስነ-ስርዓት መከበሩን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.