Fana: At a Speed of Life!

በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረትለማጠናከር የስንዴ እርሻ ልማት ትልቅ ሚና አለው – አቶ አወል

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራር በዱብቲ ወረዳ የስንዴ እርሻ ልማትን ጎብኝቷል።
 
አቶ አወል አርባ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ በክልሉ የስንዴ ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የእርሻ ልማቶች የተሻለ ምርትና ውጤት እንዲገኝ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
 
የስንዴ እርሻ ልማት በምግብ ራስን ለመቻል እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫዎት መናገራቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በሰፋፊ መሬቶች ላይ የልማት ስራዎችን በመስራት በሌሎች ክልሎችም እየተተገበረ ያለው የስንዴ እርሻ ልማት ድምር ውጤት ከስንዴ ልመና የሚያወጣ እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ ከፍታ ሊያሸጋግር የሚችል መሆኑን አብራርተዋል።
 
እየተካሄደ ባለው የስንዴ እርሻ ልማት አመራሩ ትኩረቱን ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ውጤታማ አፈፃፀም እንዲገኝ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.