Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የሚሰጥ ከ16 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ከ16 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ የብሪታኒያ መንግስት አስታወቀ፡፡

የብሪታኒያ የልማት ሚኒስቴር አንደሪው ሚሸል እንደገለፁት ፥ ድጋፉ ትግራይን ጨምሮ በድርቅ እና በግጭት ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች እንዲሁም የፀጥታ ችግር ላለባቸው አካባቢዎች የሚውል ነው፡፡

ድጋፉ ከገንዘብ በተጨማሪ በግጭት ምክንያት ለተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ምላሸ ለመስጠት የሚያስችል የምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች እርዳታ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በሚደረገው ድጋፍም ከ600 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የምግብ አቅርቦት እንደሚያገኙ ያመላከቱት ሚኒስትሩ ፥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግም ነው የጠየቁት፡፡

ከተደረገው የገንዘብ ድጋፍ 11 ነጥብ 6 ሚሊየን ፓውንድ በአምራች ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ማዕቀፍ ስር የሚካተት ነው ተብሏል፡፡

5 ሚሊየን ፓውንዱ ደግሞ በዓለም የምግብ ፕሮግራም ማዕቀፍ ውስጥ የሚሰጥ መሆኑን የብሪታኒያ መንግስት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.