Fana: At a Speed of Life!

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመርከብ መሰበር አደጋ ቢያንስ 145 ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሉሎንጋ ወንዝ ላይ በተከሰተ የመርከብ አደጋ ቢያንስ 145 ሰዎች የገቡበት አልመታወቁ ተሰምቷል፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት ፥ በሉሎንጋ ወንዝ ላይ ተሳፋሪዎችን ስታጓጉዝ የነበረቸው የሞተር መርከብ ከመጠን በላይ ሰዎችን መጫኗን ተከትሎ አደጋው መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከአደጋው 55 ሰዎች መትረፋቸውም የተነገረ ሲሆን ፥ 145 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እስካሁን አለመታወቁም ነው የተገለጸው፡፡

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባሳንኩሳ ግዛት ሌላ የትራንስፖርት አማራጭ ባለመኖሩ በአካባቢው የመርከብ አደጋ በተደጋጋሚ እንደሚከሰት አፍሪካ ኒውስ አስነብቧል፡፡

በሀገሪቱ በጥቅምት ወር በኢኩዌተር ግዛት በኮንጎ ወንዝ ላይ በተፈጠረ በተመሳሳይ ሁኔታ በተፈጠረ የመርከብ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.