Fana: At a Speed of Life!

የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን በዛሬው እለት ከሊቢያ አቻው ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ አስመልክተው  አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አማካዩ ጋቶች ፓኖም  መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ስለጨዋታው አስተያየት የሰጡት አሠልጣኝ ውበቱ፥ በሁለቱ የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደችው ሊቢያ ለኢትዮጵያ ቀላል ተጋጣሚ እንደማትሆን ገልፀዋል፡፡

ሊቢያ ነጥብ ይዛ  ለመመለስ ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች ያሉት አሰልጣኙ፥ ይህንን የመጨረሻ ጨዋታ ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

በጨዋታው ኢትዮጵያ ካሸነፈች  ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የአልጄሪያ እና ሞዛምቢክን የምድብ ጨዋታ ውጤት የምትጠብቅ ሲሆን ቀድማ መውደቋን ያረጋገጠቸው ሊቢያ ነጠብ ይዛ ወደ ሀገሯ ለመሄድ ትጫወታለች፡፡

አማካዩ ጋቶች ፓኖም በበኩሉ “የነገው ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን እናውቃለን፣ የማለፍ ዕድላችን በሌላ ቡድን ላይ ቢመሰረትም ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የተቻለንን ሁሉ በሜዳ ላይ እናደርጋለን” ብሏል።

በውድድሩ ተጫዋቾች ራሳቸውን ለማሳየት ጠንክረው እንደሚጫወቱም አመላክቷል፡፡

ብሔራዊ ቡድናችን ከሊቢያ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በአልጀሪ አናባ ባሜይ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.