Fana: At a Speed of Life!

ውጊያን በዘመናዊ የጦር መሣሪያ እና በውስን የሰው ኃይል የመጨረሰ ዐቅም እየተገነባ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓየር ኃይልና ሜካናይዝድን በማዘመን ውጊያን በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በውስን የሰው ኃይል የመጨረሰ ዐቅም እየተገነባ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በመገኘት በዓየር ኃይልና በሜካናይዝድ ተቀናጅቶ የተካሄደውን የጥምር ጦር ወታደራዊ ትሪዒት ተመልክተዋል።

እንዲሁም በቢሾፍቱ ዓየር ኃይል ዋና መምሪያ ተገኝተው በዝግጁነት ላይ የሚደረጉትን ማሻሻያዎች እንደጎበኙ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉብኝቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ፣ የዓየር ኃይል አዛዥ ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል እና ሌሎችም የመከላከያ ከፍተኛ አዛዦችና መኮንኖች ተገንኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.