Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ 27 የተለያዩ ሽጉጦችና ከ300 በላይ የሽጉጥና የክላሽን ኮቭ ተተኳሽ ጥይቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ 27 የተለያዩ ሽጉጦች እና ከ300 በላይ የሽጉጥና የክላሽን ኮቭ ተተኳሽ ጥይቶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የጦር መሳሪያዎቹ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ዛሬ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በተለምዶ ሃና ማርያም ቀጠና 3 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።

በዚህም 21 ፋልኮት፣ 6 የቱርክ ሽጉጦች፣ 245 የሽጉጥ ጥይት፣ 78 የክላሽ ኮቭ ጥይት፣ 4 የክላሽ ካርታ፣ 4 የክላሽ ማህደር እና 1 የክላሽ ሰደፍ ከሁለት ተጠርጣሪዎቹ ጋር መያዛቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የተወርዋሪ ኃይል ሻለቃ 2 ምክትል ሻለቃ መሪ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ጎሳ ከድር ገልጸዋል።

የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ለመጠበቅ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለው ተባባሪነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ መቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.