Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የ2015 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የ2015 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት በአዳማ ወረዳ ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኤልያስ ከድር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ዘመቻው በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖችና ወረዳዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በዘንድሮው የልማት መርሐ-ግብር በኦሮሚያ ክልል በተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ልማት ሥራ 3 ሚሊየን 224 ሺህ ሄክታር መሬት እና 6 ሺህ 448 ተፋሰሶችን ለማልማት መታቀዱን ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

በፀሐይ ጉልማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.