Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ከምስራቅ አፍሪካ የአይ ኤም ኤፍ ልኡካን ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ከምስራቅ አፍሪካ የአይ ኤም ኤፍ ልኡካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዛሬው ዕለት ከምስራቅ አፍሪካ የአይ ኤም ኤፍ ልኡካንቡድን አባላት ጋር በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙርያ ውይይት ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ልኡካን ቡድኑ በቆይታቸው ኢትዮጵያ የያዘችውን ለውጥ ከማሳካት አንፃር ገቢን ማሳደግ የሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በቅርበት እንደሚሰሩ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.