Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ ሀሰን ከድባጤና ቡለን ወረዳዎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በመገኘት ህዝባዊ ውይይት አካሄደ።
በዚህም ከድባጤ፣ ከቡለንና ከወምበራ ወረዳዎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ የሠላምና የልማት ሥራዎች ዙሪያ ምክክር አድርጓል።
የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ በክልሉ አሁን የተስተዋለውን አንጻራዊ ሠላም ዘላቂ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በጸጥታ ችግሩ የደረሠውን ጉዳት መልሶ ለመገንባት እየተደረገ ላለው ጥረት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
በመድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ፣ በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢስሃቅ አብዱልቃድርና የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስን ተገኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.