Fana: At a Speed of Life!

4ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ 2023 ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ200 በላይ የውጪ ኩባንያዎች የተሳተፉበት 4ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ 2023 በሚኒሊየም አዳራሽ ተከፍቷል፡፡

አውደ ርዕዩን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በተገኙበት በይፋ ከፍተዋል።

አውደ ርዕዩ ላይ የቀረቡት የግንባታ፣ የቀለም፣ የኤሌክትሪክ እና የተለያዩ የማጠናቀቂያ ግብአቶች ለዕይታ መቅረባቸውም ተመላክቷል፡፡

ይህ አጋጣሚ የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ሽግግር ከማሳለጡም ባሻገር ከውጪ ሀገራት የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝ ሚኒስትር ዴኤታው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ማምረት የሚጀምሩ ከሆነም የመንግስት እገዛና ድጋፍ እንደማይለያቸው አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.