Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች በኢትዮጵያ መካሄዳቸው ሰፊ ዕድል ይፈጥራል – ዶ/ር በለጠ ሞላ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች በኢትዮጵያ መካሄዳቸው የዓለም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ሰፊ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ገለጹ፡፡

የዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት ሶስት የተለያዩ ጉባኤዎችን በአዲስ አበባ ለማካሄድ የተቋሙ የአፍሪካ ቢሮ ዳይሬክተር አን-ራቸል አኔን ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ፥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች በኢትዮጵያ መካሄዳቸው በሀገር እድገት፣ በገጽታ ግንባታ፣ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ጉልህ አስተዋፅዖ እንዳላቸውና የዓለም ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ሰፊ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኮንፈረንስ እድሎችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የህብረቱ አመራሮች ኢትዮጵያን ተመራጭ በማድረጋቸውና ፍላጎታቸውን በመግለጻቸው አድንቀዋል ሚኒስትሩ።

ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሕዳር ወር ያስተናገደችው 17ኛው አለማቀፍ የበይነ- መረብ አስተዳደር ጉባኤ ስኬታማ እንደነበረ ጠቅሰው ፥ በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን የኮንፈረንስ እድሎች ተቀብሎ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ሁልጊዜም ዝግጁ ነን ብለዋል።

ዳይሬክተሯ አን-ራቸል ኢንኔ÷ ኢትዮጵያ ላስተናገደችውና በስኬት ለተጠናቀቀው 17ኛው የበይነ- መረብ አስተዳደር ጉባኤ አድናቆትና ምስጋናቸውን መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.