Fana: At a Speed of Life!

ከ218 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ218 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከጥር 5 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 142 ነጥብ 6 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 75 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የውጭ፤ በድምሩ ከ218 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዙን ገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ዘጠኝ ግለሰቦች እና ስምንት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ድሬዳዋ፣ አዋሽ እና ጅግጅጋ ጽህፈት ቤቶች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.