Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ከዱባይ ዓለም አቀፍ ቻምበር ጋር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለማስፋት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከዱባይ ዓለም አቀፍ ቻምበር ጋር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለማስፋት በጋራ ለመስራት ተስማምቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ÷ የዱባይ ዓለም አቀፍ ቻምበር የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ተወካይ ከሆኑት ካሊድ አል አሊ ጋር መክረዋል፡፡

በምክክሩ ጠንካራ አጋርነትን በመፍጠር የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን ለዱባይ ባለሀብቶች የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት መስማማታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም ከቀጠናው የሚመጣውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መጨመር ላይ በጋራ ለመስራትም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.